የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እግር ኳስ ክለብ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሶስት አመታት የሚቆይ የእግርኳስ ልማት ትብብር ዛሬ በአዲስአበባ ተፈራርመዋል::
የባየር ሙኒክ እግርኳስ ክለብ በተለያዩ ሀገራት የታዳጊዎች እግርኳስ ማሰልጠኛ ማእከላትን መክፈቱና ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ዛሬ ያደረጉት ስምምነት የመጀመሪ አለመሆኑም ተነግሯል ።
የባየር ሙኒክ እግርኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ባደረገው ስምምነቱ መሰረት ክለቡ የ17 አመት በታች ታዳጊዎች ማሰልጠኛ ማእከልን በኢትዮጵያ የሚከፍት ሲሆን በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን የቴክኒክ እና የአስተዳደር ባለሙያወች ተጨማሪ ስልጠናወችን በኢትዮጵያ እና በጀርመን እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ክለቡ ኢትዮጵያውያን እንደ ጀርመኖች እንዲጫወቱ ሳይሆን ያላቸውን ጥሩ ተሰጥኦ የበለጠ ለማበልጸግ መስራት ፍላጎቱ እንደሆነም ተነግሯል ፡፡
የስምምነቱን መጀመር አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሸነር እና የክለቡ ተወካዮች በተገኙበት በስምንት የአዲስ አበባ ታዳጊ ቡድኖች መካከል የእግር ውድድር ተካሂዷል፡፡
source ©Liyusport