የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ በ2017 በኢንተርናሽናል ዋና እና ረዳት ዳኝነት በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ ለተመረጡ 22 ዳኞች የባጅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል አካሄዷል፡፡ በዚሁ በዋና እና ረዳት ዳኝነት የተመረጡት፣
በኢንተርናሽናል ወንዶች ዋና ዳኛነት
1. ኃይለእየሱስ ባዘዘው
- ማሰታውቂያ -
2. ዘካሪያስ ግርማ
3. ብሩክ የማነብርሃን
4. ለማ ንጉሴ
5. በላይ ታደስ
6. ባምላክ ተሰማ
7. አማኑኤል ኃይለስላሴ
በኢንተርናሽናል ወንዶች ረዳት ዳኝነት
1. ትግል ግዛው
2. ክንዴ ሙሴ
3. ተመስገን ሳሙኤል
4. ሸዋንግዛው ተባበል
5. ኃይለራጉኤል ወልዳይ
6. በላቸው ይታየው
7. ክንፈ ይልማ
በኢንተርናሽናል ሴቶች ዋና ዳኛነት
1. ሊዲያ ታፈሰ
2. ጌራወርቅ ከተማ
3. ፍቅረገነት አሳምን
4. ጽጌ ሲሳይ
በኢንተርናሽናል ሴቶች ረዳት ዳኛነት
1. ማህሌት አስራት
2. ወይንሸት አበራ
3. ብርቱካን ለማ
4. ወጋየሁ ዘውዴ
በአጠቃላይ 22 ዳኞች የተመረጡ ሲሆን ከፊፋ የተላከውን መታወቂያ ፣ ባጅ እና ፒን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባል እና የብሔራዊ ውድድሮች አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሰሳቢ የሆኑት አቶ አበበ ገላጋይ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባል እና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሉልሰገድ በጋሻው ለኢንተርናሽናል ዋና እና ረዳት ዳኞች ሰጥተዋል፡፡