የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ማህበር በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ላደረገው መልካም ተግባር እና ጨዋታዎች ተጀምረው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቁ በማድረጉ የምስክር ወረቀት በምስጋና መልክ አበርክቶላቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ሳምንትም ከውጤት ቀውሶች ከእንቅልፉ በመንቃት ከግርጌው ከፍ በማለት ደረጃውን እያሻሻለ የሚገኘው አዲስ አዳጊው ሀድያ ሆሳዕና እንደ ሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ሁለ ባሳዩት መልካም ምግባር ነው ይህ የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው። ይህ መልካም ተግባር በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችም መተግበር እንዳለበት የማያዋላዳ ነገር መሆኑ ሀትሪክ ስፖርት ታምናለች።