ላለፉት አራት አመታት የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት በመሆን የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ ዛሬ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፍፁም ጨዋነትና ባላቸው ስነምግባር ተለይተው የሚታወቁትን የትግራይ ክልል ሴቶችን የማይገልፅና የማይወክል አሳፋሪ አስተያየት በመስጠታቸው በገጠማቸው የአፍ ወለምታ ለቀጣዩ ምርጫ የትግራይ ክልል የሰጣቸው ውክልናን ተነጥቀዋል።
ዛሬ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስፖርት የማይሽቱ ቃላትን
በመጠቀም የወከላቸውን ክልል ጭምር አንገት ያስደፍት አቶ ተኽለወይኒ ውክልናቸውን ለመነጠቃቸው ምክንያት ከሆነው የትግራይ ክልል ሴቶችን ክብር ከማይመጥነው እሳፋሪ ንግግራቸው ውጪ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ክብር የሚነካ አስተያየት መስጠታቸው ውክልናውን ለመነጠቃቸው ተጨማሪ ምክንያት ተደርጎ ተወስዳል።ላለፉት አራት ዓመታት የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ በዚህ መንገድ ዞር ማለታቸው ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ሲሆን የዚህ አይነት ስብዕና ባለቤት ሆነው ኦሎምፒክ ኮሚቴንም በምክትልነት የመምራት ሞራልም የላቸውም የሚሉ እስተያየት ሰጪዎች እየበረከቱ ነው።
የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ በአፍ ወለምታ የትግራይ ውክልናን አጡ፤የእሳቸው ውክልና መነሳት ለእግር ኳሱ መንደር ትልቅ ኦፎይታን ፈጥሯል
Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.