የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ጋር በጥምረት ከጥር 18 እስከ ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ሲያካሂድ የቆየው የጀማሪ የእግር ኳስ ጨዋታ ታዛቢነት (ኮሚሽነርነት) ስልጠና ተጠናቀቀ።
ለአሰልጣኞቹ ለአሰሰርነት ወይም ለኮሚሽነርነት ሙያ የሚያበቁ 14 ከዚህ በታች የተገለጹትን ዝርዝር መስፈርቶች
በአስስርነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፣የትምህርት ደረጃው 12ኛ ደረጃ ያጠናቀቀ እና ከዚያ በላይ፣የእንግሊዘኛ ቋንቋ የመፃፍ ፣የማንበብ እና የመናገር ችሎታ ያለው፣ኮምፒዩተር ስልጠና የወሰደ፣በፌዴራል ዳኝነት 5 ዓመታት እና ከዛ በላይ ያገለገለ፣የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚመራቸው ውድድሮች ላይ በፌዴራል ዳኝነት ላይ ለ3 ተከታታይ ዓመታት ያገለገለ የሰራ፣ዳኝነት ከአቋረጠ በኃላ ከ3 ዓመት በላይ ያልሆነው፣ስነ-ምግባሩ የተመሰገነ እና ከሙስና ወይም (ከኪራይ ሰብሳቢነት) የፀዳ፣የአይምሮ ህመምተኛ ያልሆነ፣በስፖርት ሙያ በስነ ምግባር ጥሰት ከ2 ዓመት ወዲህ ተቀጥቶ ያልታገደ፣እድሜው ከ40 ዓመት ያላነሰ ከ60 ዓመት ያልበለጠክልሉ እግር ኳስ እንቅስቃሴ ሥራ ላይ በአሰሰርነት ፣ በዳኛ ኮሚቴ አባልነት ያገለገለ እና የክልሉ ምስክርነት ያለው፣የአሰሰርነት ኮርስ ወስዶ የምስክር ወረቀት ያለው፣ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው በአሰሰርነት ሥልጠና ወስዶ በሚሰጠው ፈተና 60 ከመቶ እና ከእዛ በላይ ያገኘ፣ሁሉንም የዳኝነት ደረጃዎች ሰርተፊኬቶች ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
የሚሉትን መስፈርቶች በማዘጋጀት እና በመስፈርቱ መሠረት ባለሙያዎችን በመመልመል 93 ወንዶች እና 5 ሴቶች በአጠቃላይ ለ98 ሰልጣኞች ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1 ወንድ እና 2 ሴቶች ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞች በመሆን የአገለገሉ ፤ የቀሩት 95ቱ በፌዴራል ዳኝነት ሲሰሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ስልጠናው በኢትዮጵያዊያን የፊፋ እና የካፍ ኢንስትራክተሮች በተዘጋጀው የንድፈ ሃሳብ እና በቪዲዮ የተደገፈ ስልጠና መሠረት ያደረገ እና የታዛቢነትን /የአሴሰርነት/ ሙያን ከእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ይህንንኑ ስልጠና መሠረት በማድረግ ዛሬ ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የጽሑፍ እና የቪዲዮ መመዘኛ ፈተና ለሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ በቀጣይ ቀናት ታርሞ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡ በእለቱ ስልጠናውን የወሰዱ ባለሙያዎች የታዛቢነት ሙያን ለመስራት የሚያስችለውን ይህንን ስልጠና የአገራችንን እግር ኳስ ለማገልገል ከተለያየ ክልልና ከተማ መስተዳድር በመምጣት እንዲማሩ ላደረጉት ለኢንስትራክተሮች፣ ለዳኞች ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንዲሁም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስጋና አቅርበዋል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን ትምህርት ተግባራዊ በምታደርጉበት ወቅት በየጊዜው ሙያ የሚፈልገውን አዳዲስ ህጎችና አሠራሮች በመማማር ሙያዊ እውቀታችሁን ለማዳበር መስራት ይገባችኋል፡፡ አሰፈላጊውን ድጋፍና ሙያዊ ምክርን በተመለከተ በመማማርሃ በመመካከር ከሰልጣኞች ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኞቹ አስረድተዋል፡፡ በማስከተልም ይህ ስልጠና እንዲሳካ የበኩላቸውን ላበረከቱ በሙሉ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ለአሰለጠኑ ኢንስትራክተሮች፣ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ለሰልጣኞች ምስጋናቸውን በማቅረብ የኘሮግራሙ ፍፃሜ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳዳር ዳይሬክተር አቶ ሲያምረኝ ዳኜ ገልጸዋል፡፡