_______________________________________
ባሳለፍነው ዓመት እድሳቱን የጀመረው ኣንጋፋው ድሬዳዋ ስታድየም ጨዋታ ለማስተናገድ የሚያስችሉት ሁኔታዎች ከሞላ ጎደል ማጠናቀቅ ችሏል።የመቀመጫ ወንበር፣የመጫወቻ ሜዳ እንዲሁም የመሮጫ መም ላይ ትኩረት ያደረግው የድሬዳዋ ስታድየም እድሳት በቅርቡ ተጠናቆ ለውድድር ዝግጁ እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል።
በ1969 በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 3ኛው አፍሪካ ዋንጫ ስድስት ጨዋታዎችን ማስተናገድ የቻለው እንዲሁም በ2007 ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን የማስተናገድ ፍቃድን ከካፍ ያገኛው እድሜ ጠገቡ ድሬዳዋ ስታድየም ሙሉ በሙሉ እድሳቱን ሲጨርስ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ሚያስተናግድ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
የመጫዋቻንና መቀመጫውን በአዲስ መልክ እየቀየረ ያለው አንጋፋው #የድሬዳዋ_ስታዲየም የመጫወቻው ሜዳ ሣር ለ2ኛ ጊዜ ሰሞኑን ይታጨዳል።
የመጀመሪያ ዙር ከታጨደ በኋላ በተሻለ ሁኔታ ጥቅጥቅ ብሎ የበቀለው ሣሩ ለጨዋታ ዝግጁ ለመሆን የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በሜዳው ዙሪያ ያለው የውሃ ማሶገጃ ቦዩ በፍርግርግ ብረት የመድፈኑ ስራ የተጀመረ ሲሆን ከፈጠነ በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።
የሜዳው ሥራ ከፈጠነ በታህሳስ ወር አጋማሽ ለጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን ባለሙያዎች ተናግረዋል።፥
ምንጭ -የክለቡ የፋዊ ገፅ