13ኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ ቅዳሜ በሚደረጉ ሶስት ጨዋታወች ይጀመራል ከነዚህም ጨዋታወች መካከል ሀዋሳ ላይ በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን ሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
አርባምንጭ ከተማ በ12ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን ሲያሸንፍ፡፡ ሀዋሳ ከተማ ከ አትዮጵያ ቡና ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በተለያዩ ምክንያቶች ለሌላ ግዜ መተላለፉን ተከትሎ አለመጫወቱ ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ሀዋሳ ከተማ በሜዳው እንደመሆኑ መጠን በተጋጣሚው ላይ ድልን በማስመዝገብ ከመሪወቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ በእዮብ ማሌ የሚሰለጥነው አርባምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠናው ለመወጣት በጥንቃቄ በመጫወት ና በመልሶ ማጥቃት በሚገኙ ኳሶች ጎል አግብተው ሶስት ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
ባለሜዳወቹ ሀዋሳዎች ከደረጉት 11 ጨዋታ 13 ነጥብ በመሰብሰብ 8ደረጃን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሲቀመጡ፡፡
- ማሰታውቂያ -
ተጋጣሚያቸው አርባምንጭ ከተማ ካደረጋቸው 12ጨዋታወች 9ነጥብ በመያዝ በሊጉ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡
በሀዋሳ ከተማ በኩል ተክለማርያም፣ ሳዲቅ ሴቾ፣ ያቡን ዊሊያም ላውረንስ ላርቴ በጉዳት እና ፍሬው ሰለሞን – በቅጣት የማይሰለፉ ሲሆን፡፡
በተመሳሳይ አርባምንጭ ከተማ ወንድሜነህ ዘሪሁን፣ ወንደሰን ሚልኪያስ፣ብርሀኑ አዳሙ በጉዳት ስያጣ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ከ3 ጨዋታ ቅጣት በሃላ ወደ ሜዳ ይመለሳል፡፡
ጨዋታው በመሀል ዳኛ አርቢትር ዳንኤል ግርማይ የሚመራ ሲሆን፡፡አምና ሁለቱ ቡድኖች በሀዋሳ ስታድዬም ተገናኝተው ሀዋሳ ከተማ 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡