በኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ቀሪ 6 ጨዋታወች እሁድ ና ሰኞ በሚደረጉ ጨዋታወች ቀጥለው ሲውሉ እሁድ ከሚደረጉ 5 ጨዋታዎች መካከል አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከተማ ከመሪው ደደቢት ሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
አርባምንጭ ከተማ ካደረጋቸው ተከታታይ 3 ጨዋታወች በቅዱስ-ጊዮርጊስ በጅማ-አባጅፋር ና በወልዲያ ከተማ በመሸነፍ ለዚህ ጨዋታ የደረሰ ሲሆን፡፡
በተቃራኒው ደደቢት በተከታታይ ባደረጋቸው 3ጨዋታወች በተጋጣሚወቹ ላይ ድልን በመቀዳጀት ለዚህ ጨዋታ መድረስ ችሏል፡፡
የአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ስብስብ ደደቢት በሜዳው ሆነ ከሜዳው ውጪ ተጋጣሚውን በሚያስደነግጥ የጨዋታ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚጫወት ቡድን ሲሆን ከመሀል ተመስርተው በሚሄዱ ኳሶች በአጥቂወቹ ጌታነህ ከበደ ና አቤል ያለው አማካኝነት በሚቆጠሩ ጎሎች ነጥብ ይዘው ሲወጡ ተመልክተናል፡፡
በአንፃሩ አዞዎች በጥቂት ተጫዋቾች የግል ብቃት በስተቀር በተዳከመ የጨዋታ ና የቡድን እንቅስቃሴወች እንዲሁም በቁልፍ ተጫዋቾች ጉዳት ታጅቦ በተደጋጋሚ ሽንፈት በማስተናገድ በወራጅ ቀጠናው ሊገኝ ችሏል፡፡
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ከአሰልጣኝ አንስቶ እስከ ቴክኒክ ኮሚቴ ድረስ ለውጥ በማድረግ የነገውን ጨዋታ የሚጫወት ሲሆን በዋና አሰልጣኝነት የተሾሙት እዮብ ማሌ ና ምክትሉ ማትዮስ ቀድመው ከነበሩበት ክለብ ጋር ባለባቸው ጨዋታ ምክንያት በዚህ ጨዋታ ላይ አይገኙም፡፡የነገውን ጨዋታ በአንበሉ አማኑኤል ጎበና ና በግብ ጠባቂው ጃክሰን ፊጣ እየተመራ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
ከአርባምንጭ ከተማ በኩል በጉዳት ተሾመ ታደሰ፡ተካልኝ ደጀኔ፡ታዲዮስ ወልዴ እና ግብ ጠባቂው አንተነህ መሳ አንዲሁም ኦፕራሲዮን የተደረገው ወንደሰን ሚልኪያስ ከሜዳ ረዘም ላለ ጊዜ እንደ ሚርቅ ሲገለፅ ወንድሜነህ ዘሪሁን ከጉዳቱ በማገገም ለጫወታው ሲደርስ፡፡ አጥቂውን ገ/ሚካኤል ያዕቆብ በወልድያው ጨዋታ ቀይ ካርድ በመመልከቱ በቅጣት አይገኝም፡፡
በደደቢት በኩል ከተከላካዩ ብርሀኑ ቦጋለ የጉዳት ዜና ውጪ የቅጣትም ሆነ ተጨማሪ ጉዳት የለም፡፡
ደደቢት ካደረጋቸው 9 ጨዋታወች 19 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃው ሰንጠረዥ አናት ላይ ሲቀመጥ፡፡
አርባምንጭ ከተማ በተመሳሳይ ከደረጋቸው 9 ጨዋታወች 6 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃው ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሁለቱ ቡድኖች አምና ተገናኝተው በአርባምንጭ በኩል ወንድሜነህ ዘሪሁን እንዲሁም በደደቢት በኩል ጌታነህ ከበደ ባስቆጠሩት ግቦች 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡