የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ለአራት ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች ሲራዘም 6 ወራትን ማስቆጠሩ የሚታወቅ ነው፡፡
መራዘሙን ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት የአለም አቅፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ (ፊፋ ) ተወካዮችን ወደ አዲስ አበባ ልኳል፡፡
የፊፋ ቸወካዬች በጁፒተር ሆቴል ከአምስቱ ዕጬ ፕሬዝደንቶች እና ከዘጠኝ አስመራጭ እና ሶስት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንዲሁም ከጊዜያዊ ዋና ፀሐፊው አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ጋር ጥልቅ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውይይቱ ላይ የአስመራጭ ኮሚቴው ከዚህ ቀደም ያቀረባቸውን ቅሬታዎች በጥልቀት በመመርመር የፊፋ ተወካዮች ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል፡፡
የፊፋ ተወካዮች ለ4 ጊዜ የተራዘመውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንት እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ከዛሬ ጀምረው ጉዳዩን በማጣራት ምርጫው ለመጨረሻ ጊዜ የሚካሄድበትን ቀን ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡