የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማህበር /ፊፋ/ ጋር በተመተባበር ለ35 ኢንተርናሽናል እና ኤሊት ፌደራል ዳኞች የአዘጋጀው የከፍተኛ የእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና /FIFA MA ELITE REFEREE’S COURSE/ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በጁፒተር ሆቴል ይካሄዳል፡፡ የመክፈቻው ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት መሆኑን እየገለጽን የስፖርት መገናኛ ብዙሃን ኘሮግራሙ ላይ በመገኘት እንዲዘግቡ ተጋብዘዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተላከ ኢ-ሜይል