የፋሲል ከነማና የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጨዋታ የቀን ለውጥ ተደረገበት
እሁድ እለት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የፋሲል ከነማና የወልዋሎ አዲግራት ጨዋታ ወደ ሰኞ ተዛውሯል፡፡
ወልዋሎዎች ትላንት ሀዋሳ ላይ በሲዳማ ቡና 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ከተሸነፉ በኋላ ። ከሀዋሳ አዲስ አበባ በመመለስ ወደ ጎንደር የሚያደርገው ጉዞ ረጅም በመሆኑ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ጨዋታው ወደ ሠኞ ሊዛወር ችሏል፡፡ ይሀን ጨዋታ ፌዴራል አርቢትር ተፈሪ አለባቸው ይመራዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡