ጌታቸው ዳዊትን በአሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኃላ የአምስት አዳዲስ ተጨዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቁት ደደቢቶች አምና በደካማው ቡድን በግሉ ጥሩ የተንቀሳቀሰውን መድሃኔ ብርሃነ ለቀጣይ ሁለት ዓመት ከክለቡ ጋር ሚያስቀጥለውን ውል አስፈርመውታል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከደደቢት ሁለተኛ ቡድን ደደቢትን የተቀላቀለው መድሃኔ የቀኝ መስመር ተከላካይ፣የመስመር አጥቂ አንዲሁም የፊት አጥቂ በመሆን አናት ክለቡን አገልግሏል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበው አዲስ የውድድር ፎርማት ውድቅ መሆኑን ተከትሎ በየትኛው ሊግ አንደሚሳተፍ ያላወቀው ደደቢት በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ዝውውሮችን ለማጠናቀቅ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።