በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ማይገኙት ሻምፒዮኖቹ ዳንኤል ደምሱን አስፈርመዋል።
የጋብርኤል መሀመድን ቦታን ለመሸፈን በርካታ ተጨዋቾችን ለሙከራ ያመጡት መቐለ 70 አንደርታ በመጨረሻም የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ና ወልድያ ከተማ አማካይ ማስፍረም ችለዋል።በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ዳንኤል ደምሱ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ጥሩ ጅማሮ ቢያሳይም ከዲድየር ጎሜዝ ስንብት በኃላ አብዛኛውን ጊዜ ከመጀመርያ ተሰላፊዎች ውጪ በመሆን አሳልፏል።
በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር አራት ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ምዓም አናብስቶቹ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጨዋቾን ለማስፈረም በንግግር ላይ ናቸው።