አስቀድመው ስምምነት የተደረሰባቸው የሁለቱ ተጫዋቾች ውል መቋጫውን አግኝቷል፡፡ ዘንድሮ ከሀዲያ ሆሳና ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረውና አምና የድሬ ከነማ ተጫዋች የነበረው የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ መሄዲን ሙሳ ለ1 ዓመት ሲፈርም ፡፡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢሸፍቱ ኦቶሞቲቭ በ2011 ደግሞ ለኢትዮጵያ መድን በመጫወት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው የቀኝ ተከላካዩ ያሲን ጀማል ደግሞ ለ2 ዓመት ፊርማውን አኑሯል፡፡
አቅም ያላቸውን የድሬዳዋ ልጆች በቡድን ውስጥ ለማቀፍ እቅድ የያዘው ክለቡ ከሁለቱ ተጨዋቾች በተጨማሪ ሌሌች አቅም የላቸውን ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድን እንዲሁም በቅድመ ዝግጅት ወቅት በሙከራ ከሚታዩ ተጫዋቾች በመለየት በቡድኑ ውስጥ እንደሚያካትቱ ተጠቁሟል፡፡
Via – dire kenema offical page