በዮውሃንስ ሳህለ እየተመራ ስምንት ተጨዋቾችን ያስፈረመው ድሬዳዋ ኣሁንም በተመሳሳይ መቐለ ላይ ከቡድኑ ጋር የሙከራ ጊዜ ሲያሳልፍ የነበረውን ኢታሞና ኮሚኔን ማስፈረም ችሏል።ባለፈው ውድድር ዓመት ኣጥቂ መስመር ላይ ክፍተት የታየባቸው ድሬዎች ችግሩን ለመቅረፍ በ2017/18 ውድድር ዓመት በናሚብያ ሊግ እና ዋንጫ 19 ጎሎች ያስቆጠረው ኮሚኔ በቋሚነት ኣስፈርሟል።
በተያያዘ ዜና የቀድሞው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኣዲስ ኣበባ ከተማ ተጨዋች ሀይሉ ነጋሽ ሌላኛው የዮውሃንስ ሳህለ ኣዲስ ፈራሚ በመሆን ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል፤እንዲሁም ከደደቢት ግብ ጠባቂ ምንተስኖት የግሌን ማስፈረም ችሏል።
መስከረም 26 ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው ትግራይ ዋንጫ ሚሳተፈው ድሬዳዋ እንደ ኣዲስ እየተገነባ ያለውን ቡድኑን ኣቋም ሚፈትሽበት ጥሩ ኣጋጣሚ ይሆናል።