አዳማ አበበ በቂላ እስታዲየም ላይ አዳማ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥተዋል።
ከማሊያና ከተለያዮ ጉዳዮች ምክኒያት ዘግይቶ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የተቀዛቀዘ የመጀመሪያ አጋማሽ ሲያስመለክት ጎል በማስቆጠሩ ረገድ ቅድሚያውን የያዙት አዳማ ከተማዎች ሲሆኑ ጥሩ ብቃት ላይ እሚገኘው ዳዋ ሁቴሳ በ54’ኛ ደቂቃ ላይ ባለሜዳዎቹን መሪ መድረግ ሲችል።
በተቃራኒው አባጅፋሮች አቻ ለመሆን 12’ደቂቃዎችን ለመጠበቅ ሲገደዱ በ66ኛ ደቂቃ ላይ ባሳለፍነው ክረምት ከድሬዳዋ ከተማ ያስፈረሙት ይሁን እንዳሻው አባጅፋሮች ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ እሚያስቸላቸውን ግብ ማስቆጠር ችሏል።
በሌላ የሊጉ የመርሀ ግብር ጨዋታ አሰልጣኙን ያሰናበተው ወልዋል አዲግራትን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን የ2-0 ውጤት ማሳካት ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ለድሬ ከተማ በ5’ኛ ደቂቃ በአትራም ኩዋሜና ጨዋታው ሊጠናቅቅ በሚጠበቅበት ሰዕት መሀመድ ጀማል ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል።
ሊጉ ነገም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት ከመከላከያ ምሸት 11 ሰዓት ይጫወታሉ።
ደረጃ ሰንጠረዥ
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”1″ align=”right”]