በዛሬው እለት የተደረገው ይህ ስምምነት የደጋፊ ማህበር ምዝገባን, የተለያዩ ክፍያዎችን መክፈል የአባልነት መዋጮን ጨምሮ, ወርሀዊ እና አመታዊ የኮከብ ተጫዋቾች ምርጫን, በክለቡ ዙርያ የተለያዩ ዜናዎችን እና መረጃዎችን በቀላሉ ለደጋፊው የሚያቀርብ የዲጅታል ሲስተም ሲሆን ይህም ስምምነት የክለቡን ተደራሽነት እና መረጃዎችን በቀላሉ እንዲደርስ የሚረዳ ይሆናል
ስራውም በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን ይህንንም ጉዳይ አስመልክቶ ስለ አጠቃቀሙ እና ሙሉ ስራው በቅርቡ የሚገለፅ ይሆናል::