በቅርቡ ከዳንኤል አጃይ ጋር የተለያዩት ጅማ አባጅፋር መሀመድ ሙንታሪን ማስፈረም ችለዋል።
ጳውሎስ ጌታቸውን በአሰልጣኝነት በመቅጠር አዲስ ቡድን እየገነቡ ሚገኙት ጅማዎች ከዚህ ቀደም ለአሻንቲ ኮቶኮቶ፣ማዴማ፣ሉሳካ ዳይናሞስ መጫወት የቻለውን መሀመድ ሙንታሪን በማስፈረም ዳንኤል አጃይ ትቶት የሄደውን ክፍተት መድፈን ችለዋል።የ27 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ከ20 ዓመት በታች ና ከ23 ዓመት በታች የጋና ብሄራዊ ቡድን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ከአሻንቲ ኮቶኮቶ ጋር የጂኤፍኤ ስፔሻል ዋንጫን(GFA Normalization Special Cup 2019)ማንሳት ችሏል።
የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በጅማ አያካሄዱ እሚገኙት ጅማ አባጅፋሮች ጥቅምት 23 በሚጀምረው አዳማ ሲቲ ካፕ ላይ በመሳተፍ ለ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሚዘጋጁ ይሆናል።