የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ የምን ግዜም ኮከብ ጎል ኣግቢ የሆነው ጌታነህ ከበደ(ሰበሮም) በኢትዮጵያ ክለቦች ደረጃ ሦስተኛ ክለቡን ቅዱስ ጊዮርጊስን በሁለት ዓመት ውል ፈርሟል።በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት በኣጥቂ ቦታ ችግር የታየባቸው ጊዮርጊስ ጌታነህን ማስፈረማቸው ችግሩን እንደሚቀርፍላቸው ይታመናል።በደቡብ ኣፍሪካ ለቢድቬድ ቪትስ እና ዩኒቨርስቲ ፕሪቶርያ የተጫወተው ጌታነህ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የተዋወቀው በ2002 በደቡብ ፓሊስ ማልያ ነበር፤በተዋወቀበት ዓመትም የውድድሩ ኮከብ ጎል ኣስቆጣሪ በመሆን ኣጠናቅቋል።