የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የምክትል አሰልጣኞቻቸውን (Coaching Staff) በመምረጥ ከዚህ ቀደም አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ (ቲጋናን) አሁን ደግሞ የአካል ብቃት አሰልጣኝነትን ጨምሮ ለያዘው ይታገሱ እንዳለን በም/አሰልጣኝነት ለ2 አመት አፄዎቹን ተቀላቅሏል፡፡
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ ከ1992 ዓ/ም ጀምሮ አዳማ ከነማ ታዳጊና ዋናው ቡድን እንዲሁም በተለያዩ አመታት መተሀራ ስኳር፣ ወንጂ ስኳር፣ ሀረር ከተማ በተጫዋችነት ያሳለፈ ሲሆን በድጋሚ አዳማ ከነማን ለ5 አመት በአንበልነት እየመራ በመጫዎት ከፍተኛ ልምድን ያካበተ ነው።
ይታገሱ በአሰልጣኝነት ሂወት በአዳማ ከነማ u-17 ተስፋ ቡድንና በታዳጊ (B) ቡድን ውስጥ በማሰልጠን ለዋናው ቡድን ተጨዋቾችን በማሳደግና በውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ ክብሮችን አግኝቷል። በአዳማ አመለሸጋው እያሉ የሚጠሩት ይታገሱ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ጥሪ ተቀብሎ ፋሲል ከነማን በመቀላቀል ፊርማውን አስቀምጧል።