ትናንት ሰበታ ላይ በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ወላይታ ዲቻ ከፋሲል ከተማ ባደረጉት ጨዋታ የጦና ንቦቹ በእዮብ አለማየሁ የሀትሪክ ግቦች 3-0 አፄዎቹን ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ፋሲል ከተማዎች በትናንተናው ጨዋታ በወላይታ ድቻ በኩል ተሰለፎ የተጫወተው ተጨዋች ሙባረክ ሽኩር ከዚህ በፊት፡ከመከላከያ፡ሀዋሳ ከተማ፡ መቆለ ከተማ፡ከኢለክትሪክና አርባምንጭ ከተማ ጋር ክለቡ ባደረጋቸው ጨዋታዎች 5 ቢጫ ካርድ ሞልቶት የትናንትናው ጨዋታ ሊያልፈው የሚገባና በደንቡ መሰረት ለፌዴሬሽኑ የቅጣት ክፍያ ሳይከፍል በትናንትናው ጨዋታ ለክለቡ ግልጋሎት መስጠቱ ተገቢ አይደለም በሚል ዛሬ የፋሲል ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ክስ አስገብቷል፡፡
ክለቡ አያይዞም የትናንትናው ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድመን ተጨዋች ሙባረክ ሽኩር መሰለፉ ተገቢ አለመሆኑን ክስ አስመዝግበናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጉዳዩን አጣርቶ ተጨዋቹ 5 ቢጫ ካርድ እያለበት መሰለፉ እውነታ ከሆነ ውጤቱ በፎርፌ አፄዎቹ ሊያሸንፉ ይችላሉ፡፡በሌላ በኩል የፋሲል ከተማ ክስ እውነት ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ገቢ ይሆናል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የጉዳዩን ግብረ መልስ አጣርተን በዚሁ በገፃችን የምንዘግብ ይሆናል፡፡