ታህሳስ 17፣ 2009
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት.ማልማትና ማስፋፋት የስራ ሂደት ኃላፊ እንደነበሩ እሚታወስ ነው፡፡
አቶ ዱቤ ጅሎ የስራ መልቀቂያ የዛሬ አመት ታህሳስ 23 ቀን 2008 ዓ.ም ደብዳቤ በማስገባት ከጥር 1 ቀን2008 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ እንደማይኖሩና በምትካቸው አዲስ ባለሙያ እንዲቀጥር በመጠየቅ መሰናበታቸውን እሚታወስ ነበር።
በአዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኘሬዘዳት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ማልማትና ማስፋፋት የስራ ሂደት ኃላፊ አቶ ዱቤ ጅሎን ወደ ቀድሞ ስራቸው መልሷል፡፡ከዛሬ ታህሳስ 17 ቀን ጀምሮ ሰራቸውን መጀመራቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡