የኢትዮጵያ ቡና የስፖርት ክለብ ባደረገው ግምገማ በጊዚያዊነት ቡድኑን ከኒቦሳ ቩሲቪችን ተረክበው ሲያሰለጥኑ የነበሩት አሰልጣኝ ገዛህኝ ከተማ ከሀላፊነት በማንሳት ምክትል አሰልጣኙ እድሉ ድረጄን በጊዜአዊነት ሿሟል።
ኢትዮጵያ ቡና በአመቱ መጀመሪያ ወደ ክለቡ ያመጣቸው አሰልጣኝ ኒቦሳ ቩሲቪች በክለቡ ቆዬታቸው በሊጉ ከ9 ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ የቻሉት ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፋቸው ተከትሎ ነበር ጥር 1 ቀን 2009 ዓ .ም አሰልጣኙን አሰናብቶ የዛሬውን ተሰናባች አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማን መሾሙ እሚታወስ ነው ፡፡