በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሊጉ መሪዎች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ከሜዳው ውጭ ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 1 ተለያይቷል። ጋዲሳ መብራቱ ሀዋሳ ከተማን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በ15ኛው ደቂቃ
ሲያስቆጥር ራምኬል ሎክ ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል።
ደደቢት እና መከላከያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።
በተመሳሳይ ፋሲል ከተማ ከሜዳው ውጭ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ተጫውቶ 0 ለ 0 አቻ ተለያይተዋል።
- ማሰታውቂያ -
9 ስአት ላይ ከተጀመሩት አራት ጨዋታዎች በድል የተጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና ከጂማ አባቡና ያደረጉት ግጥሚያ ነው። ኢትዮጵያ ቡና አስቻለው ግርማ በ68ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ ወላይታ ዲቻን 2 ለ 1 አሸንፏል። ወልድያ ከተማ ትናንት በይፋ በተመረቀው ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገው ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።
ትናንት በተደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች መሪው አዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 0 ተሸንፏል። ሲዳማ ቡና በበኩሉ ለስምንተኛ ጊዜ ሽንፈት ያስተናገደውን አዲስ አበባ ከተማ 1 ለ 0 ረቷል።
ደረጃ ሰንጠረዥ
# ክለብ ተጫ ልዩ ነጥብ
1 ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 12 21
2 አዳማ ከተማ 11 4 21
3 ደደቢት 11 7 20
4 ፋሲል ከተማ 10 6 19
5 ሲዳማ ቡና 11 1 18
6 አርባምንጭ ከተማ 11 2 17
7 መከላከያ 11 -1 16
8 ኢትዮጵያ ቡና 11 -1 16
9 ወላይታ ድቻ 10 1 15
10 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10 0 12
11 ወልድያ 11 -3 11
12 ኢትዮ ኤሌክትሪክ 11 -3 10
13 ድሬዳዋ ከተማ 11 -6 10
14 ጅማ አባ ቡና 11 -5 9
15 ሀዋሳ ከተማ 10 -6 7
16 አዲስ አበባ ከተማ 11 -8 5
—————————————————————————————————————————-
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
ደረጃ ተጨዋች ጎል
1 ጌታነህ ከበደ 10
2 አዳነ ግርማ 5
3 ሳላዲን ሰኢድ 4
4 ፍሬው ሰለሞን 4
5 ፍፁም ገብረማርያም 4
6 ገብረሚካኤል ያዕቆብ 4
7 ኤዶም ሆሮሶውቪ 4
8 ወንድሜነህ ዘሪሁን 3
9 ፒተር ኑዋዲኬ 3
10 ምንይሉ ወንድሙ 3
11 ጃኮ አራፋት 3
12 ሐብታሙ ወልዴ 3
13 ሙጂብ ቃሲም 3
14 በዛብህ መለዮ 3
15 አቡበከር ሳኒ 3