የዘጠነኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ማገባደጃ የሆነው የወልዲያ ና የአርባምንጭ ከተማ የጨዋታ መርሀግብር ሰኞ በወልድያው ግዙፉ ስታድዬም ይካሄዳል፡፡
የአሰልጣኝ ዘማርያም ስብስብ የሆነው ወልድያ ከተማ አዳማ ላይ ከተቀዳጀው የመክፈቻው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር ድል በሃላ ማሸነፍ የተሳነው ሲሆን በ3 አቻ እና በ2 ተሸነፎ በ6 ጨዋታ 14 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ያሰናበቱት አርባምንጭ ከተማዎች በተመሳሳይ ካደረጉት ጨዋታዎች 1ማሸነፍ ሲችሉ 4ተሸንፈው በ3 አቻ ወቶ በጎል ክፍያ ተበልጦ በ6 ነጥብ 15 ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡
ለ2ኛ ጊዜ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ብድኑን በመረከብ ስራውን የጀመረው ምክትል አሰልጣኙ በረከት ደሙ የመጀመሪያ የ2010 ጨዋታን ያደርጋል፡፡
ወልድያ ከተማ በሜዳው እንደመሆኑ መጠን ሙሉ ሀይሉን በማጥቃት እንደሚጫወት ሲጠበቅ፡፡ አርባምንጭ ከተማ ባንፃሩ በመከላከል ና በመልሶ ማጥቃት ውጤት ይዞ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱም ብድኖች በተመሳሳይ የውጤት ቀውስ ውስጥ ሚገኙ ሲሆን ይህን ጨዋታ መሸናነፍ ከቻሉ በትንሹም ቢሆን እፎይታን ሚያገኙ ይሆናል፡፡ የዛሬ አመት በዚህ ሜዳ ተገናኝተው 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በወልድያ በኩል
ብሩክ ቃልቦሬ ና አማረ በቀለ በቅጣት ከሰኞው ጨዋታ ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በአርባምንጭ ከተማ በኩል አርባምንጭ በጉዳት ወንድሜነህ ዘሪሁን ፡ ወንደሰን ሚልኪያስ ፡ አማኑኤል ጎበና ፡ ተሾመ ታደሰ፡ሲያጣ ከቅጣት አንድነት አዳነ ይመለሳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች የዛሬ ዓመት 2009 ዓ.ም 17ኛ ሳምንት ላይ ተገናኘተው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡