በ2004 ከፕርሚየር ሊጉ ወርዶ ሶስት ዓመት በብሄራዊ ሊግ የሰነበተው ድሬደዋ ከነማ በ2008 ወደ ፕርሚየር ሊግ ተመልሶ ከመጣ በሁዋላ በአሰልጣኝ መሰረት ማኔ, ዘላለም ሺህፈራው እና ስምኦን አባይ እየተፈራረቀ ያልተረጋጋ ቡድን ሆኖ ቆይቷል፡፡ ክለቡ ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን በሚሻሻል የኮንትራት ስምምነት ለአንድ ዓመት አስፈርሟል፡፡ ለመኖርያነት ደረጃው የላቀ ሆቴልን ጨምሮ አስፈላጊ ጥቅማጥቅሞች የተሟላለት ዮሃንስ 1.3 ሚሊዮን ብር የፊርማ እንዲሁም ወርሃዊ 60ሺህ ብር ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሰሓሌ ከጅማ አባጅፋር ጋር በቃል ደረጃ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ማረፊያቸው ድሬዳዋ ከተማ ሆኗል
ድሬደዋ ከተማ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ሾሟል።።
Hatricksport team