ጅማ እባጅፋር ጳውሎስ ጌታቸውን በዋና እሰልጣኝነት ቀጠረ
በቅርቡ ባህርዳር ከተማን የለቀቀው ጳውሎስ ጌታቸው(ማንጎ) እምና ከዘማርያስ ጋር ከተለያየ በኃላ በጊዜያዊ እሰልጣኝ ሲመራ የነበረውን ጅማ እባጅፋርን ለማሰልጠን ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ከባህርዳር ጋር ጥሩ ሚባል ዓመት ያሳለፈው ጳውሎስ ጌታቸው ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የፋይናንስ ቀውስ እና የወሳኝ ተጨዋቾቹን ማጣት የታየበትን ጅማ እባጅፋር የማሻሻል ከባድ ስራ ይጠብቀዋል።
ጠጣር የተከላካይ ክፍል በመገንባት ሚታወቀው ጳውሎስ ጌታቸው እምና በተደጋጋሚ በእንድ ጨዋታ ብዙ ግቦችን ሲያስተናግድ የነበረውን የጅማ እባጅፋር ተከላካይ ክፍልን እንደገና በእዲስ ተጨዋች ሊያዋቅረው እንደሚችል ይገመታል።