ኢትዮጵያ ቡና ብስራት ገበዩን ከወልቂጤ በማስፈረም የክረምቱን ፈራሚዎች ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።
ዘግይቶ ወደ ዝውውሩ የገባው ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን በአምበልነት በመምራት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳለፈውን ብስራት ገበየሁን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል ።ቡናዎች ብስራት ገበየሁ የክረምቱ ስድስተኛ ፈራሚያቸውን ሲያደርጉ በቀጣይ ቀናትም የአዳዲስ ተጨዋቾች ፊርማ በተጨማሪም የነባር ተጨዋቾች ውል በማራዘም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።