በአሸናፊ በቀለ እሚመሩት አዳማ ከተማ ዮናስ በርታን ከደቡብ ፖሊስ አስፈርመዋል።በአሰልጣኝ አብርሃም መብራህቱ ጥሪ ተደርጎለት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የሚገኘው ዮናስ በርታ አምና ከደቡብ ፖሊስ ጋር በግሉ ጥሩ አመት ማሳለፍ ችሏል።
አዲስ ህንፃን ያጡት አዳማዎች ዮናስ በርታን ማስፈረማቸው መሃል ሜዳ ላይ ያላቸውን የተጫዋች አማራጭ ሊያሰፋላቸው አንደሚችል ይገመታል።
በቅርቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት አዳማ ከተማዎች በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ ዝውውሮች የማጠናቀቅ እድላቸው ሰፊ ነው።