ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ታህሳስ 26/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተ. ዳኛ ባምላክ ተሰማ
ቦታ: አዲስ አበባ ስታድየም
6ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስን መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ፍፃሜውን ያገኛል። መቐለ 70 እንደርታዎች ከጣፋጭ የትግራይ ደርቢ ማግስት፣ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተካታታይ የነጥብ ማጣት ጉዞ ሚያገናኘው ይህ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳስሰነዋል።
መቐለ 70 እንደርታ ከቡድኑ አምበል ሚኪኤለ ደስታ ወጪ በጉዳት ሆነ በቅጣት ሚያጡት ተጨዋች አይኖርም።ባሳለፍነው ሳምንት ወልዋሎን ባሸነፋበት ጨዋታ በጉዳት ተቀይሮ የወጣው ዳንኤል ደምሱ ከጉዳቱ አገግሞ ለጨዋታው ዝግጁ ሆኗል።ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ግብ ጠባቂው ልአለም ብርሃኑ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣አቡበከር ሳኒ አሁንም ከጉዳታቸው አለማገገማቸውን ተከትሎ ከነገው ጨዋታ ውጪ ሲሆኑ ሳላሀዲን በርጌቾ፣ሳላሀዲን ሰይድ እና ፓትሪክ ማታሲ ወደ ልምምድ ተመልሰውላቸዋል።
ቀጥተኛ እና መስመር ላይ ትኩረት ያደርገ አጨዋወትን ለመተግበር ሚሞክሩት ፈረሰኞቹ መስመር ላይ ትኩረት አድርገው እድሎችን መፍጠር ሊማክሩ እንደሚችሉ ይገመታል።በተለይ በ5 ጨዋታዎች ስድስት ግቦች ያስተናገደውን የመቐለ 70 እንደርታ ደካማ የመከላከል ቅንጅትን ሰብሮ ለመግባት ከመሀልብ እና ከመስመር የሚጣሉ ኳሶች ላይ ትኩረት ያደርግሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
መቐለዎች ከወልዋሎ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ከጉዳት ተመልሶ ጥሩ የተንቀሳቀሰውን ዮናስ ገረመውን ማግኘታቸው በአማኑኤል እና ያሬድ ከበደ ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን የቡድኑ እድል የመፍጠር ሀላፊነት በመጠኑም ሊቀንስ ችሏል።ከሜዳቸው ውጪ ሲጫወቱ የመልሶ ማጥቃትን አጨዋወት ተመራጭ ሚያደርጉት መቐለዎች ዛሬም በጥሩ አቋም ላይ በሚገኙት ያሬድ ከበደ ና አማኑኤል ገብረሚካኤል ላይ መሰረት ያደርገ መልሶ ማጥቃት አጨዋወትን ይዘው የመግባታቸው እድል ሰፊ ነው።በተለይ በሁለቱ ተጨዋቾች ያለው መግባባት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ ክፍል ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
መቐለ 70 እንደርታ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ላይ 5 ግቦችን አስቆጥሮ አራት ግቦችን ሲያስተናግድ ፈረሰኞቹ በበኩላቸው በሜዳቸው ባደረጉዋቸው ሁለት ጨዋታዎች 1 ግብ አስቆጥረው ምንም ግብ አልተቆጠረባቸውም።