የፕሪምየር ሊጉ የሚሳተፉ የትግራይ ክልል ክለቦች በየካቲት 8 ካፕ መቐለ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።
የትግራይ ህዝብ የደርግ መንግስትን ለመጣል ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባበት አርባ አምስተኛ አመት የምስረታ በአል ምክንያት በማድረግ የካቲት ወር ላይ የሚደረገው የየካቲት 11 ካፕ ላይ በፕሪምየር ሊግ የሚሳቱፉ ሶስት ክለቦች እና አንድ የከፍተኛ ሊግ ክለብ እንደሚሳተፉበት ታውቋል። በዚህም መሰረት የሊጉ መሪው መቐለ 70 እንደርታ እና ተከታዩ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ እና ከአስከፊ የውድድር አመቱ አጀማመር ወደ ጥሩ ውጤት እየመጣ የሚገኘው ስሑል ሽረ እና አምና ከፕሪምየር ሊጉ የተሰናበተው ደደቢት መሆናቸው ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። ውድድሩ መች መካሄድ እንደሚጀምር የታወቀ ነገር የለም።