በ26ኛ ሳምነት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሲካሔድ የመጀመሪያው ጨዋታ የነበረው በ8፡30 በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደው
በኢትዮጵያ ቡና እና በጅማ አባ ቡና በኩል የተደረገውጨዋታ ነበር ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ በቅርቡ ሂወቱ ላለፈው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ቢኒያም የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎለታል ።
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው ከተጀመረ ቡሃላ የታየው እንቅስቃሴ ብዙም ማራኪ አልነበረም በጨዋታው ላይ ጅማ አባ ቡናወች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ቢያደርጉም ወደጎል በሚደረጉ ሙከራወች የታጀበ አልነበረም። በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱ ቡድኖች መጀመሪያ ከነበረው የተሻለ እንቅስቃሴ እና የጎል ሙከራዎችን ማሳየት ችለው ነበር ሆኖም ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ቀርተው ነጥብ ተጋርተው ሊወጡ ችለዋል።
በሻምፒዮንነት ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሲዳማ ቡና በሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘውን አዲስ አበባ ከተማን አስተናግዶ በሊጉ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ማለት የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል። በጨዋታው መጀመሪያ አዲስ አበባ ከተማዎች ጨዋታውን መቆጣጠር ችለው ነበር ጨዋታው በተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ በአጥቂው ሃይሌ እሸቱ አማካኝነት መምራ ችለው ነበር ሆኖም መሪነታቸውን አስቀጥለው መቆየት የቻሉት እስከ 37ኛው ደቂቃ ብቻ ነበር በ37ኛው ደቂቃ በናይጄሪያዊው ላኪ ሳኒ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ አቻ ሆነው ለእረፍት ወደ መልበሻ ቤት ገብተዋል። ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡናዎች የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይተዋል በ 48ኛው ደቂቃም ላኪ ሳኒ ለራሱም ለቡድኑም 2ኛውን ግብ በማስቆጠር ሲዳማ ቡናን መሪ ማድረግ ችሏል። በ61ኛው ደቂቃላይ አዲስ ግደይ ቡድኑ ሲዳማ ቡና መሪነቱን ያሰፋበትን 3ኛ ጎል በራሱ የግል ጥረት አስመዝግቦ ቡድኑንአሽናፊ አድርጎታል።
በሌላ ጨዋታ 9ሰአት ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ 1 እኩል በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ በጨዋታው ቅድሚያ ግብ ማስቆጠር የቻሉት ንግድ ባንኮች በ56ኛው ደቂቃ ላይ በጂብሪል አህመድ አማካኝነት ነበር ሆኖም መደበኛው 90ደቂቃ አልቆ በተጨመሪ 2ደቂቃ ታፈሰ ተስፋዬ ባስቆጠረው አንድ ግብ ሁለቱ ክለቦች ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል። በጨዋታው ላይ ደጋፊወች ” ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ከሙስና የፀዳ ትውልድ እናፍራ ” የሚል ባነር በስታዲየም ውስጥ አሳይተዋል።
በ10:30 በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያ እና ደደቢት ባደረጉት ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታው መከላከያ የተሻለ የኳስ እንቅስቃሴ ማሳየት ችሎ ነበር። ሆኖም የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው በመከላከያ በኩል በ87 ደቂቃ አወል አብደላ የቢጫ ካርድ ሰለባ ሲሆን በደደቢት በኩል ብርሃኑ ቦጋለ በ45ኛው ደቂቃ ሰለሞን ሃብቴ በ63ኛው እንዲሁም ሺመክት ጉግሳ በ76ኛው ደቂቃ የቢጫ ካርድ ሲመለከቱ ዳዊት ፍቃዱ በ82ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ከጨዋታው መጠናቀቅ ቡሃላ ጨዋታውን ማሽንፍ ትችሉ ነበር ነጥብ ተጋርታችሁ መውጣታችሁ ተገቢ አይደለም በሚል ምክንያት የተናደዱ አንዳንድ የሲዳማ ቡና ደጋፊወች ባነሱት ፀብ ምክንያት በተወረወሩ ድንጋዮች የመከላከያ ተጨዋቾች የሚጠቀሙበት ሰርቪስ መስታወት ተሰብሯል።