ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን የወላይታ ድቻው ልዩነት ፈጣሪ ቸርነት ጉግሳ እንግዳችን ነው….ከሀትሪክ ጋር ቆይታ አድርጓል.. በርካቶች አሞግሰውታል በርታ ብለውታል እሱ ግን አልረካም 5 ግብ ብቻ አስቆጥሬ የምን ርካታ ነው? የሚለው ቸርነት ” ዘንድሮ ምንም የሰራሁት ነገር የለም የኔ ምርጥ አቋም
ገና ወደፊት የሚመጣው ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…በየትኛው ክለብ ማሊያ ይሆን…?
*….ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ባልተለመደ ሁኔታ ለአራት አመታት ዋንጫ ጠፍቷል ኮከቦች ይገባሉ ለውጥ የለም… አሁን ግን ለውጥ ያስፈልጋል የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክለቡ የቦርድ አባል “ጠንካራ ተፎካካሪና የዋንጫ ቡድን ሆነን ለመቅረብ ውስጣችንን እየፈተሽን ነው”ሲሉ ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
*…. አሁንም ወላይታ ድቻ ቤት ጩኸት
አለ…. የክለቡ ተጨዋች የነበረውና በራሱ ወጪ ህክምና ላይ የነበረው አስናቀ ሞገስ ” የወጪውን ደረሰኞች ከወሰዱ ቢቆዩም ያወጣሁትን ገንዘብ አልተኩልኝም ዝምታቸው ተገቢ አይደለም” ሲል ወላይታ ድቻዎች ላይ ያለውን ቅሬታ ገልጿል…
*…. የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ… “በአዲሱ አሰልጣኝ መሻሻል አመጣን እንጂ የተመዘገበው ውጤት ለኛ በቂ አይደለም”ሲል ለሀትሪክ ተናግሯል…
*…..መከላከያ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል…”መከላከያ ትልቅ ቡድን ነው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም በመመለሱ ተደስቻለሁ” ሲል የክለቡ ተጨዋች በሃይሉ ግርማ አስተያየቱን ሰጥቷል…..
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*….. የአውሮፓ ዋንጫ ከተጀመረ ሳምንት ሞልቶታል…”አንድ የተለየ ነገር መስራት እፈልጋለሁ” ሲል ለዋንጫ ከተገመቱት ቡድኖች መሃል አንዱ የሆነው የጣሊያን /አዙሪዎቹ/ አለቃ ሮቤርቶ ማንቺኒ ተናግሯል….
*…”ለፖርቱጋል ለመጫወት ማለም የጀመርኩት ከ2004 ጀምሮ ነው፥ ለሀገሬ መጫወት ትልቁ ህልሜም ነበር” ሲል የማን.ዩናይትድና የፖርቱጋል ኮከብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተናግሯል…
*…. የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ኮከብ ጁድ ቢሊንግሃም “ለሀገሬ ብሄራዊ ቡድን እጫወታለሁ ብዬ ባላስብም ህልሜ ግን እውን ሆኗል” ሲል በእንግሊዝ ሶስቱ አናብስት ውስጥ መካተቱ የፈጠረለትን ደስታ ገልጿል..
*….ዘንድሮ ላሊጋውን አጥቷል እሱ ግን ያልማል…አንቷን ግሪዝማን “ላሊጋን ከባርሴሎና ጋር የአውሮፓ ዋንጫን ደግሞ ከፈረንሳይ ጋር የማሳካት ህልም አለኝ” ሲል ተናግሯል……
*…. በነገው ዕትማችን አጫጭርና በርከት ያሉ የዝውውር መረጃዎችን ይዘናል….
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……