ለኮትዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 11 በደቡብ አፍሪካ እና በላይቤሪያ መካከል ተደርጎ 2 – 2 የተጠናቀቀውን ጨዋታ ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ በብቃት መርቶታል ።
ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ በጨዋታው ለላይቤሪያ ሁለት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርድ አሳይቷል ።
በጨዋታው በአምላክ ተሰማን ጨምሮ አራቱም ዳኞች ከኢትዮጵያ የነበሩ ሲሆን በመስመር ዳኝነት ተመስገን ሳሙኤል እና ፋሲካ ብሩ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ቴዎድሮስ ምትኩ መርተውታል ።
በተያያዘም የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) በትናንትናው ዕለት ይፋ ባደረገው የ25 ኤሊት ኤ ዳኞች ዝርዝር ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ አካቷል ።
- ማሰታውቂያ -
ካፍ በዝርዝሩ 25 ዳኞችን ያሳወቀ ሲሆን ከመጪው ሚያዝያ ስድስት እስከ ሚያዝያ አስር በካይሮ የስልጠና ቆይታ እንደሚኖራቸው ተገልጿል ።
📸 ©Getty images