መቀሌ 70 እንደርታ ከድሬዳዋ ከተማ
መቀሌ 70 እንደርታ
አራተኛ የአመት የፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎውን በማድረግ ላይ ያለው ቡድኑ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ያስመዘገበው አምስት ነጥብ ከሶስቱ አመታት ዝቅተኛው ነው
በፕሪሚየር ሊጉ አስቀድሞ ግብ ባስቆጠረባቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው አንድ ጊዜ ብቻ ነው(በ2010 የውድድር ዘመን 28ኛ ሳምንት በሲዳማ ቡና 2 – 1)
- ማሰታውቂያ -
በሊግ ታሪኩ በ1 – 1 ውጤት ከተለያየባቸው ስድስት ጨዋታዎች ቀጥሎ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው አንድ ጊዜ ብቻ ነው
በውድድር አመቱ አራት ጨዋታዎችን ካደረጉ ክለቦች መካከል ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባህርዳር ከተማ ጋር ዝቅተኛ ግብ ያስቆጠረው ቡድን ነው(3 ግቦች)
በሊጉ ባደረጋቸው የአምስተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች በአንድ አሸንፎ ፣ በአንድ አቻ ሲለያይ በአንዱ ተሸንፏል
በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች 100 ለማድረስ 5 ግቦች ይቀሩታል (95 ግቦች)
ድሬዳዋ ከተማ
በፕሪሚየር ሊግ ታሪኩ በመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎች ከፍተኛውን ነጥብ አስመዝግቧል (7 ነጥቦች)
በፕሪሚየር ሊጉ በመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎች ሽንፈት ያላስተናገደው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
የዛሬው ጨዋታ 360ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው ነው
ባለፉት ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስተናገደ ሲሆን ይህም በ2015 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ 15 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ካስተናገደበት በኋላ ከፍተኛው ነው
ባለፉት ሰባት የውድድር አመታት የዓመቱ አራተኛ ጨዋታዎች በሁለቱ ብቻ ሲያሸንፍ ሁለቱም ጅማ አባጅፋርን ነው
ቻርለስ ሙሴጌ ለድሬደዋ ከተማ በሊጉ 60ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
እርስ በርስ
በሊጉ ከዚህ ቀደም በአምስት ጨዋታዎች ተገናኝዋል
መቀሌ 70 እንደርታ በሶስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ ድሬዳዋ ከተማ አሸንፏል
በነዚህ ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር ድሬዳዋ ከተማ አራት ግቦችን አስቆጥሯል
በመጨረሻው የእርስ በርስ ግንኙነተቻው ድሬዳዋ ከተማ 1 – 0 አሸንፏል