በ ፋሱ (FASU) ኣስተባባሪነት የሚዘጋጀው የመላ ኣፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታዎች 9ኛው ውድድሩን በመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣዘጋጅነት ይካሄዳል።በ1971 በ10 የኣፍሪካ ሃገራት የተመሰረተው ፋሱ (FASU) የመጀመርያ ውድድሩን 1975 ኣክራ ጋና ላይ ኣካሂዷል ከዛ በመቀጠልም በ ናይሮቢ 1978-79 ሲያካሂድ፤ሦስተኛው ውድድሩን በ 1982 ሉሳካ ላይ ሊያካሄድ ፕሮግራም ቢያዝለትም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ ቀርቷል፤ ውድድሩ ከ 22 ዓመታት መቋረጥ በኃላ በ2004 በናይጀርያ ባኡቺ ኣስተናጋጅነት እንደገና ተጀምሯል፤ ከ 2010 ውጪ በየሁለት ዓመት ልዩነት እየተካሄደ ይገኛል።
ከ18 የኣፍሪካ ሃገራት 58 የኣፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ሚሳተፋበት የዘንድሮ ውድድር ዛሬ በትግራይ ስታድየም በደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በይፋ ተጀምሯል።ውድድሩ ከሰኔ 24-29 በተለያዩ ውድድሮች ታጅቦ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጃቸው ደረጃቸውን በጠበቁ የመወዳደርያ ማእከላት ይካሄዳል።