አቤል እንዳለ….
….ኢት.ቡና vs ድሬዳዋ ከተማ…
የሚገርም ገጠመኝ ያለው ዝውውር ነው….ድሬዳዋ ከተማ ከአቤል እንዳለ ጋር ተስማምቷል…በቅድሚያ ክፍያም ሆነ በሚከፈለው የወር ደመወዝ ዙርያ ተስማምተዋል።
- ማሰታውቂያ -
….ግን ድንገት እንዲህ ሆነ…
አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ አቤልን ለማስፈረም ላንቻ ወደሚገኘው የፈረሰኞቹ ጽ/ቤት ደብዳቤና የሚያስፈልገውን ፎርማሊቲ ለማሟላት አቤልና አሰልጣኙ በተለያየ መኪና ጉዞ ጀመሩ ቢሮው አካባቢ ሲደርሱ የአቤል መኪና የለም…ቢጠበቅም አልደረሰም ወደ አቤል ቢደወል ስልኩ ዝግ ነው…
…አቤል ከበደና ድሬዳዋ ከተማ….
ተጨዋቹ ውሉን ለማደስ ከአሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ ጋር ተነጋግሯል..ከክለቡ የቀረበለትን ጥያቄ ግን ውድቅ አድርጓል
ለቀጣዮቹ 3 አመታት ውሉ እንዲታደስ ክለቡ ያቀረበለት የደመወዝ ጥያቄ ግን ቀልድ ሆኖበታል…ለ3 አመት በወር 60 ሺህ ብር እየከፈልንህ ተጫወትልን የሚለው የኢትዮዽያ ቡና ጥያቄ ለተጨዋቹ ስድብ ነበር… ከውሉ አለመስማማት ቀጥታ ያመራው ፈላጊ ወደ ሆነው ሌላው ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ነበር ወዲያውኑ ነው የተስማማው…
ለ2 አመት ወደ 130 ሺህ ብር ለመክፈል የቀረበውን የድሬዳዋዎች ጥያቄን ተቀብሎ ለመፈረም ተስማማ…
…አቤል እንዳለና አቤል ከበደ….
የሁለቱ አቤሎች ግጥምጥሞሽ ያስገርማል…አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ አቤል ከበደን ውል ለማጸደቅ ወሎ ሰፈር ወደሚገኘው የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሲደርስ ካልጠበቀው እውነት ጋር አይኑ ተገጣጠመ…. ሊያስፈርመው የፈለገውና ስልኩ የተዘጋበት አቤል እንዳለ ከኢትዮዽያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር ውሉን ለማጸደቅ ወደ ፌዴሬሽኑ ሲገቡ ፊት ለፊት ተገጣጠሙ…. ለካ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለመግባት ከጫፍ የደረሰው ጉዞ የከሸፈው መሃል ላይ የተደወለው የካሳዬ ስልክና ባደረጉት ውይይትም ካሳዬና አቤል ለመስማማት በመቻላቸው ነው ካሳዬና ዘማርያም ሰላምታ ተለዋውጠው ይዘዋቸው የመጡትን ሁለቱን አቤሎች ይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ…
ሁለቱም አቤሎች በተለያየ የጉዞ አቅጣጫ ሆነው ቀስ እያሉ ዘማርያምና ካሳዬን በጨረፍታ እያዩ ወደ ውስጥ ዘለቁ….
… የአንድ ቀኑ ገጠመኝ ይህን ይመስላል….