ሰበታ ከተማን በሊጉ የማቆየት ሃላፊነት ወስዶ ክለቡን ከእቅዱ በላይ ውጤታማ ያደረገው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ መዳረሻው ባህርዳር ከተማ የሆነ ይመስላል።
የአሰልጣኙ ስም ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከአዳማ ከተማ፣ ከባህርዳር ከተማና ከሰበታ ከተማ ጋር ቢያያዝም ከሰሞኑ አዲስ አበባ ከነበሩት የባህርዳር ከተማ አመራሮች ጋር መስማማቱ እየተነገረ ነው።
ከሰበታ ከተማ ጋር ሀምሌ 30/2013
ድረስ የውል ስምምነት ያለው ኢንስትራክተር አብርሃም ከነሀሴ 1 ጀምሮ ባህርዳር ከተማን ለማሰልጠን ተስማምቷል።
አሰልጣኙን ለማግባባት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት የክለቡ አመራሮች ባቀረቡለት አጓጊ እቅድና ጥያቄውን ባቀረበለት እንቢ የማይባል እንግዳ ምክንያት መስማማቱ ተነግሯል።
በጉዳዩ ዙርያ ክለቡና አሰልጣኙ ይፋዊ መግለጫ ባይሰጡም በፋይናንስ ጠንካራ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በ2014 ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን እየሰራ መሆኑ ታውቋል።