አቡበከር ናስር ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን በአንድ አመት በሚቆይ ውል መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ተጫዋቹ ወደ ማሚሎዲ ሰንዳውንስ ካመራ በኋላ በጉዳት ምክንያት የተጠበቀውን ያህል እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግሮ ቆይቷል።
ማሚሎዲ ሰንዳውንስም የውጭ ሀገራት ተጫዋቾች ኮታን ከአቡበከር ናስር ውጪ ሙሉ ማድረጉን ተከትሎም የተጫዋቹ ማረፊያው ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ሆኗል።
አቡበከር በማሚሎዲ ሰንዳውንስ ቆይታው በ18 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ አራት ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወቃል።
- ማሰታውቂያ -
የቀድሞው የፊት አጥቂ ተጫዋች ፍቅሩ ተፈራ እ.አ.አ በ2010/11 የውድድር ዘመን በሱፐርስፖርት ዩናይትድ ተጫውቶ አሳልፏል።
የሶስት ጊዜያት የደቡብ አፍሪካ ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ሱፐርስፖርት ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አራት ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ ከ16 ክለቦች የ13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።