ለ12 አመታት ያህል ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተው ምንተስኖት አዳነ ለአዳማ ከተማን ለመጫወት ተስማምቷል። ከደቂቃዎች በፊት በተገኘ መረጃ ተጨዋቹ ለቀጣዮቹ 2 አመታት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።
ተጨዋቹ ፈረሰኞቹን ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን አምበልነት ያገለገለ ሲሆን 7 የፕሪሚየር ሊግ፣2 የአሸናፊዎች አሸናፊ፣2 የኢትዮዽያ ዋንጫን ጨምሮ ወደ 17 ዋንጫዎችን አሳክቷል። ሰኔ መጨረሻ ውሉ መጠናቀቁ ተከትሎ ጊዮርጊሶች ውሉን ባለማደሳቸው የቀድሞ አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝን ተከትሎ ወደ አዳማ ከተማ ማቅናቱ ተረጋግጧል።