በተጠናቀቀው የዉድድር አመት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ መሰናበቱን ተከትሎ ምክትል አሰልጣኝ የነበረዉ ይታገሱ እንዳለ ክለቡን በጊዜያዊነት በአሰልጣኝነት እየመራ የመጨረሻዎቹ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ነጥቦችን በመሰብሰብ ቡድኑን ከመዉረድ ስጋት አላቆ በ35 ነጥቦች 11ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ማስቻሉ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ የክለቡ አመራሮች አሰልጣኝ ይታገሱን በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸዉ ተረጋግጧል። በተያያዘም ክለቡ በቀጣይ አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ይረዳዉ ዘንድ በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ዝዉዉር ገበያዉ በመግባት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እንደሚቀላቀሉ ተጠቁሟል።