በ2014 ዓመተ ምህረት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጨረሻው ቀን በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ ዘግይቶም ቢሆን ወደ ዝውውር መስኮቱ ገብቷል ።
ከሳምንታት በፊት አሰልጣኝ ይተገሱ እንዳለን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው ክለቡ አምስት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ።
መስዑድ መሀመድ ፤ ዊልያም ሰለሞን ፤ አድናን ረሻድ ፤ ቦና አሊ እና ሰዒድ ሀበታሙ አዳማ ከተማን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው ።
በተጨማሪም የቀኝ መስመር ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል ።