በርካታ ተጫዋቾቻቸውን ያጡት አዳማ ከተማዎች በወጣቶች ላይ ተስፋውን ያደረገውን አሰልጣኝ ክለቡን እንዲመራ መርጠዋል ።
በአዳማ ከተማ ያለፉትን ዓመታት በምክትል አሰልጣኝነት ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ አስቻለው ሀይለሚካኤልን ዋና አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸው ታውቋል ።
አሰልጣኝ አስቻለው ሃይለሚካኤል ከወራት በፊት ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ በወጣቶች የተገነባ እና ጠንካራ ተፎካካሪ ቡድንን ይዘው እንደሚቀርቡ መግለፃቸው የሚታወስ ነው ።