➢…ም/ል አሰልጣኙ ይታገሱ እንዳለ ይመራዋል….
ላለፉት ዘጠኝ ወራት አዳማ ከተማን ሲያሰለጥን የነበረው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24 ጨዋታዎች ለ14 ኛ ጊዜ አቻ ወጥቶ ከትላንት በስቲያ በባህርዳር ከተማ ጋር የተሸነፈው የአዳማ ከተማ አመራሮች ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ለመለያየት በመወሰን ካነጋገሩት በኋላ ዛሬ በስምምነት ተለያይተዋል።
የክለቡ አመራሮች ዛሬ ጠዋት ተጨዋቾቹን በማነጋገር ከቀጣዩ የሰበታ ከተማ ጨዋታ ጀምሮ ቡድኑን ምክትል አሰልጣኙ ይታገሱ እንዳለ እንደሚመራው መግለጻቸው ታውቋል። በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቀው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በበኩሉ ” ከአመራሮቹ ጋር ውይይት አድርጌያለሁ የምፈልገውን ነግሬያቸው የነሱን ምላሽ እየጠበኩ ነው ከዚያ ውጪ በይፋ ተሰናብተሃል አልተባልኩም” ሲል ያለውን ሁኔታ አስረድቷል።
- ማሰታውቂያ -
አዳማ ከተማ በ27 ነጥብ ካለበት 13ኛ ለመውጣት በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ እየተመራ ዘመቻውን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል