16ኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ በድምቀት ይጀመራል። በኤልያና ሞል ዛሬ በወጣው የእዚሁ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ላይም ውድድሩ በሁለት ምድብ በመከፈል የሚጀመር ሲሆን የመክፈቻ ተጋጣሚዎቹም ቅዳሜ በ8 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በ10 ሰዓት ቅ/ጊዮርጊስ ከመቻል በሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል።
ይኸው ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲጀመርም የመግቢያ ዋጋዎቹ ሚስማር ተራ 20 ብር፣ ካታንጋ 30 ብር፣ ከማን አንሼ 50 ብር፣ ጥላፎቅ 100 ብር እና ክቡር ትሪቩን 200 ብር ሆነዋል።
ምድብ አንድ
1. ኢትዮጵያ ቡና
2. ኢትዮ ኤሌክትሪክ
3. ለገጣፎ ለገዳዲ
ምድብ ሁለት
1. ቅ/ጊዮርጊስ
2. መቻል
3. ኢትዮጵያ መድን