“ከተመሠረተ 60 አመት ቢሞላውም የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማርኬቲንግ ዲፓርትመንት አልነበረውም መኪናም የለውም” ሲል የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።”
ፌዴሬሽኑ ከዳሽን ባንክ ጋር በቤስት ዌስተርን ሆቴል በጋራ በሰጡት መግለጫ ከገቢና ከጠንካራ የማርኬቲንግ ስራ አንጻር ምንም መስራት እንዳልቻሉ ከ60 አመት ታሪክ ውስጥ ምንም አሁንድረስ የራሱ መኪናና ጠንካራ የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት አለመኖሩ ከገቢ አንጻር ችግር መፍጠሩና ለማስተካከል ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመራሮቹ አስረድተዋል።
ስለውድድሩ የተናገሩት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አስራት ሃይሌ በበኩላቸው የኤርትራ ክለቦች ፍቃድ በማጣትና የሱዳን ክለብ በግሉ መምጣት ባለመቻላቸው በኢትዮጵያዊያን ክለቦች መሃል የሚደረግ ጨዋታ መሆኑን ገልጸውበተተኪነት ጅማ አባጅፋርን አግኝተናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም በኛ በኩል የሲቲ ካፑ ገቢ ለፌዴሬሽኑ የአመት እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ብዙ ሮጠናል ብዙ ፊት አይተናል ልፋታችን ተሳክቶ ያሰብነውን እንደምናሳካ ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
“በውድድሩ የአሞሌ ሽያጭ ዛሬ የጀመረ ሲሆን ፌዴሬሽኑ አስሶ አስሶ መርጦ የመጣው እኛ ጋር ነው ለዚህም እናመሰግናለን የስፖርት ቤተሰቡ ከኮቪድ የማይጠቃበትና የማይንገላታበት እንደሚሆን ርግጠኛ ነን” ሲሉ አስረድተዋል።
አጠቃቀምን በተመለከተ የዳሽን ባንክ ተወካዮች እንዳሉት “በቴሌግራም ፕላትፎርም ቲኬት መቁረጥ ይችላል ይህን ማድረግ ካልተቻለ በየባንካችን በመሄድ ቲኬቱን መቁረጥ ይችላል ለዚህም በራችን ክፍት ነው ሁሉም የዳሽን ቅርንጫፎች ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ፌዴሬሽኑ እንደገለጸው ከቲኬት ሽያጭ ጋር ተያይዞ ከዳሽን ባንክ ጋር በመነጋገር የመፍትሄ አቅጣጫ እንዳስቀመጡና ከኮቪድ መከላከል ጋር ተያይዞ ጠንካራ ስራ መሠራቱን አስረድተዋል። ከኮከብ ተጨዋች አንጻር ጠንካራ ስራ በመስራት በየ ጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ይኖራል ከሁሉም በላይ ደግሞ ከገቢው ጋር ተያይዞም ለመከላከያ ሰራዊት ከገቢው አንጻር ድጋፍ አናደርጋለን ብለን ወስነናል ሲሉ ገልጸዋል።