የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በካሜሩን አስተናጋጅነት ለ33ኛ ጊዜ በሚደረገዉ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የዕጣ ማዉጣት ስነስርዓት በዛሬዉ ዕለት ያዉንዴ በሚገኘዉ ፓሌስ ዴ ኮንግረስ እንደሚካሄድ ታዉቋል።
በኢትዮጵያ በኩል በዚህ የዕጣ ማዉጣት ስነስርዓት ላይ ለመታደም የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና ፀሀፊዉ አቶ ባህሩ ጥላሁን ወደ ስፍራቁ የተጓዙ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ደግሞ በአዳማ ይገኙ የነበሩት የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ወደ ያዉንዴ እንደሚያመሩ ይጠበቃል።
በካሜሩን የ2022 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የ24 ሀገራት የምድብ ድልድል ቋት ከቀናት በፊት ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ኢትዮጵያም በቋት አራት ከሱዳን ፤ ማላዊ ፤ ኮሞሮስ ፤ ከኢኳቶሪያል ጊኒ እና ከጋምቢያ ጋር ትገኛለች።