በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኘው የቡርኪናፋሶ ብሄራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል ። በካሙ ማሎ የሚሰለጥነው ቡድን በአቡ ዳቢ ዝግጅቱን እያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት በምድብ ስድስት ከቱኒዚያ ፤ ማሊ እና ጋምቢያ ጋር ከተደለደለው የሞሪታንያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን አድርጎ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይቷል ።
በአፍሪካ ዋንጫው ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶ ጥር 5 ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።