በቀጣዩ ወር ላይ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሐራዊ ቡድን ከግብፅ አቻዉ ጋር በሜዳዉ ለሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ የተመረጠዉ የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በካፍ ባለሙያዎች ግምገማ ተደርጎበታል።
ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በሜዳዋ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል እና የካፍን ሚኒማ የሚያሟላ ስታዲየም ስለሌላት በሚል በሜዳዋ ማድረግ የሚገባትን ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ ማለትም በደቡብ አፍሪካ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።አሁን ደግሞ በቀጣዩ ወር መገባደጃ ላይ ለሚደረገዉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳዉ እንዲጫወት እና የካፍ አመራሮችን ዝቅተኛ መስፈርት እንኳን ለማሟላት ረብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የመጫወቻ ሜዳዉ እጅግ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ስለመዘጋጀቱ የመልበሻ ክፍሎቹም ላይ በተቻለ መጠን ማስተካከያ በማድረግ ላይ እንደሆኑ እና በዚህም የካፍ አመራሮች ደስተኞች መሆናቸዉን ነገር ግን ስታዲየሙ ብቁ ነዉ አይደለም የሚለዉን ከቀናት በኋላ ካፍ ባለሙያዎቹ ያቀረቡለትን ሪፖርት ተመልክቶ ካፍ ዉሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።