በተለያዩ ትልልቅ የእግርኳስ የውድድር መድረኮች ላይ ሀገሩን ኢትዮጵያ በመወከል በበጎ መልኩ በማስጠራት የሚታወቀው ባምላክ አሁን ደግሞ በካሜሩን አስተናጋጅነት በሚደረገዉ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በዳኝነት ከሚሳተፉት መካከል አንዱ በመሆን መመረጡ ታዉቋል።
በዛሬዉ ዕለት በካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመዳኘት የተመረጡት የመጨረሻ ስልሳ አራት ዳኞች ዝርዝር ይፋ ሲደረግ፤ ከነዚህም መካከል ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ አንዱ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፤ በዉድድሩ ላይም ባምላክ በቫር ዳኝነት እንደሚያገለግል ተገልጿል።
በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ በመድረኩ ላይ ከዋልያዎቹ በተጨማሪም በኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የምትወክልም ይሆናል።